Blog

Articles, reflections and public-health writing by Dr Nebiyu Lera Alaro.

Former Prime Minister Haile Mariam Dessalegn

ደፋሩ ጀግና፦ ክቡር የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

በዋናነት በአማርኛ የተጻፈ፣ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን አመራር፣ ዲፕሎማሲና ብሔራዊ የልማት ታሪክ የሚያስታውስ የምስጋና ጽሑፍ። የደራሲው የራሱ አስተያየት ነው።

ይህ ገጽ በደራሲው የዎርድ ሰነድ የቀረበውን የአማርኛ ጽሑፍ ይይዛል። የደራሲው የአስተያየት ጽሑፍ እንጂ ይፋዊ መግለጫ አይደለም።

ዋናው የአማርኛ ጽሑፍ

ደፋሩ ጀግና፦ ክቡር የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

#ያልተዘመረለት ጀግና

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያከናወኗቸው ተግባራት!!

በኢትዮጵያ ታሪከ ሠላማዊ ትግል በማካሄድ ከዩኒቨርሲት መምህርነት እስከ ሀገር መሪነት ድረስ ደረጃ በደረጃ ራሱን እያሳደገ የመጣ የተማረ መሪ መሆኑ በራሱ አኩሪ ታሪክ ነው፣

መለስ ዜናዊ በሞት ከዚህ ዓለም በተለየበት ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ መደናገጥ በፈጠረበት ወቅት በሀገር ያጠላውን የተስፋ መቁረጥ ስሜት ያለመለመ ህይውት የዘራ መሆኑ በራሱ ታሪክ የማይረሳው ሀቅ ነው፣

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርነት ቦታ በመያዝ የአፍሪካ ህብረት 2063 አጀንዳ ውጤታማ ሆኖ እንዲቀረጽ ያስቻለ፤ የህብረቱ 50ኛ ዓመት ወርቅ ኢዩበልዩ በዓል ለቀጣይ አፍሪካ ተስፋ በሠነቀ መልኩ እንዲከበር ያደረገ የአፍሪካ ፋና ወጊ ነው፣

ለዘመናት የነበረውን የሻከረ የግብጽን ግንኙነት ዓለምን ባሰደመመ መልኩ ሠላማዊ አድርጎ የአባይን የፖለቲካ ጡዘት አደብ ያስገዛ ጽንፍ ያያዙ የግብጽ ፖለቲካ መሪዎችን በዲፕሎማሲ ብልሃትና ህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማሳመን ግድቡ ያለምንም መወላዳት እንዲቀጥል በሳል አመራርና ሙያዊ ድጋፍ የሰጠ ጀግና ነው፣

ትልቁ ችግር የሙስና፣ የብልሹ አሠራርና የመልካም አስተዳደር ችግር ነው ብሎ በሀገር ደረጃ የመልካም አስተዳደር ችግር በማስጠናት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ለህዝብ በይፋ የአመራር በኔት ወርክ መተሳሰር፣ የሀገር ልጅ የወንዝ ልጅ ማለት በአቻ ጋብቻ መሥራት ችግር አለ ብሎ ለህዝብ ያረጋገጠ ቅን የህዝብ ልጅ ነው፣

ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የሳበች ባለ ተስፋ ሀገር እንድትሆን በማስቻል ብዙዎችን እጃቸውን በአፋቸው ያስጫነ ነው፣

ለዘመናት የተተበተበውን የአዲስ አበባ ውሃ ችግር በዘላቂ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ አመራርና ሙያዊ ድጋፍ የሰጠ የለውጥ ሐዋርያ ነው፣

የባበቡር ፕሮጀክቶችን ፈር በማስያዝ መርቶ ለዚህ ያደረሰን ዘመን ያፈራው መሪ ኢንጂነር ነው፣

ኢትዮጵያ ገና ነቅታለች የተባለውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሀሳብ ከማመንጨት እስከ አመራር በመስጠት በዓለም ትልቅ ፕርጀክት የታባለውን የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጨምሮ ሌሎች ያስገነባ የትራንስፎርሜሽን መሪ ነው፣

ዛሬ ሀገርቷ የደረሰችበት ሁኔታ በጫካ ትግል የሚመራ ሳይሆን የምሁራንን ሙያዊ እውቀት የሚጠይቅ ነው በማለት ብዙ ምሁራን በሀገርቱ አሻራቸውን እንዲያስቀምጡ መንገድ ያበጃጀና ተግባራዊ ያደረገ ተራማጅ ሰው ነው፣

የፖለቲካ ምህዳር በማስፋት የተዘጋውን በር ሁሉን ከፍቶ ለህዝብ ዴሞክራዊያዊ ትግል መንገድ የቀየደ ባለመንገዴ ብዙ ነው፣

የወጣቶች ተደማጪነት የግድ ይላል በማለት በር የከፈተና ወጣቱ በጥይት ሳይሆን በሃሳብ ጥይት ትግል ማካሄድ እንደሚችል ያረጋገጠ የኢትጵያ ወጣቶች አባት ነው
“
“
“
ስለሆነም የአቶ ኃይለማርያም ታሪክ ሠሪነት ቀጥሎ የአፍሪካ መሪዎች የአልጋ ቁረኛ የደዌ ዳኛ ሆነው፣ ህዝባቸው የደም እምባ እየዘራ ቅጠል እየበላ ከወታደሩ ጋር በዱር በጫካው እየተዋደቀ ሥልጣን እንዲለቁ ተጠይቆ እንኳን ሥልጣን አልለቅም ብሎ ህዝባቸውን በሚፈጁበት አፍሪካ፣ የኢትዮጵያ ኢህአዴግ ውስጥ መሆን ዴሞክራት መሆኑን ያረጋገጠ በይፋ ለህዝብ አሳውቆ ሥልጣን መልቄቅ በራሱ ታሪክ ነውና ታሪክ ይዘክር……ማን ያውቃል የኢትዮጵያ ታሪክ ፀሐፊዎች ካልጠመሙ በስተቀር ሀይለማርያም ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ታሪክ ሠርቶ ታሪክ ያስረከበ ታሪካዊ ጀግና መሪ ነው……….ተወደደም ተጠላ ሀቁ ይህ ነው!!!

ረጅም ዕድሜና ዘላቂ ጤንነት ለመሪያችን!!!

#ያልተዘመረለት brave hero #ያልተዘመረለት.

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

“
“
“

ረጅም ዕድሜና ጤና ለረጅም ጤናማ ሕይወት!!!

ተዛማጅ መረጃ

Select your language

ፕሮፌሰር ነቢዩ ለራ በመስመር ላይ
👋 ሰላም! መልእክትዎን ከታች ይጻፉ፤ ለሙያዊ ጥያቄ በዋትስአፕ ይከፈታል።